የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ክልል አቀፍ የአመራር የዉይይት መድረክ እያካሄደ ነዉ
መጋቢት 6/2017 ዓ.ም
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በቀጣይ ወራት በሚከናወኑ ዕቅድ ዙሪያ ክልል አቀፍ የከፍተኛ አመራር የዉይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል ።
በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ ፣የዉስጥ አንድነትን በማጠናከር የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
ለዚህም በቀጣይ ጊዜያት የሚከናወኑ ተግባራትን በአግባቡ በመምራት ያሉትን ሁሉንም አማራጮች መጠቀም እንደሚገባም ነዉ ርዕሰ መስተዳደሩ የገለፁት ።
መድረኩ በክልሉ በቀጣይ ሶስት ወራት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ትኩረት ያደረገ ስነድ በክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ቀርቦ ዉይይት የሚደረግ መሆኑ ተመላክቷል።
በመድረኩም ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ ፣የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ አለማየሁ ባዉዲን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ።
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE