የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
ጳጉሜን 3/2017 ዓ.ም
2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ በአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ወርቅህ ገበየሁ (ዶ/ር) እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት አመራሮች በጉባዔው እየተሳተፉ መሆኑን የኢቢሲ መረጃ ያመለክታል። ጉባዔው “ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ማፋጠን፡ የአፍሪካን አረንጓዴ ልማት በፋይናንስ መደገፍ" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል።
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE