• Call Us
  • +251..........

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኦሞ ዞን የስራ ቆይታ በማድረግ ላይ ይገኛሉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኦሞ ዞን የስራ ቆይታ በማድረግ ላይ ይገኛሉ 

ርዕሰ መስተዳድሩ ለይፋዊ የስራው ጉዳይ ዲመካ ከተማ ሲደርሱ በክልሉ የጂንካ ማዕከል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤ በደቡብ ኦሞ ዞን አመራሮች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎችና በከተማዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡   

ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ በሚኖራቸው ቆይታ ከኬንያ ከተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች በቀጠናው ሰላም እና ደህነት እና በአካባቢው የጋራ ልማት ዙሪያ የጋራ ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል ። 

ከዚህም ባለፈ በዞኑ በዳሰነች ወረዳ፤ የኦሞ ወንዝ በኦሞራቴ ከተማ ላይ የደቀነውን የጎርፍ አደጋ ስጋት ለመቀልበስ በመከናወን ላይ የሚገኙ ስራዎች ምልከታ የሚያደርጉ ሲሆን፤ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በመደረግ ላይ ባለው ጥረት ዙሪያም ከህብረተሰቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚመክሩ ይሆናል፡፡ 

የክልሉ መንግስት የኦሞ ወንዝና የቱርካና ሐይቅ ሙላት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ በአካባቢው የደቀኑትን የጎርፍ አደጋ ስጋት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
  
ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የኬኒያ  እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።