"ዮ ማስቃላ ፍትህ የሚሰፍንበት በጎነት የሚለመልምበት በዓል ነው" -ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ
የጋሞ ህዝብ ዘመን መለወጫ የ''ዮ ማስቃላ በዓል በአርባምንጭ ከተማ ተከብሯል ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ በዓሉ ልዩነት የሚቀርፍ አንድነት የሚያጎላ ነው ብለዋል።
ማስቃላ በጎነት የሚለመልምበት ፍትህ የሚሰፍንበት መሆኑን የገለፁት አቶ ጥላሁን በውስጡ ያሉ የፍትህ ስርዓቶች አብሮነትን እንደሚያጠናክሩ ጠቁመዋል ።
ባህላዊ ዕሴቶች የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚያጠናክሩ በመሆናቸው በትውልድ ውስጥ እንዲሰርፁ በትኩረት እንደሚሰራ ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል ።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ የማንሰራራት ጉዞ ላይ መሆኗን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ፣በዓሉ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበት ወቅት ላይ መከበሩ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
የተጀመሩ ድሎችን በቀይ ባህር መድገም ይገባል ያሉት አቶ ጥላሁን ለዚህም የጋራ ጥረት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል ።
በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ የክልሉ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል ።
የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) ዮ ማስቃላ የብዙሃነት ማሳያና የአንድነት ምልክት ነዉ ብለዋል።
ጋሞ ዘይሴና ግድቾ በጋራ የሚያከብሩት በዓል መሆኑን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ይህንኑ ለማልማት በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል ።
በበዓሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስቴር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ፤የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባዉዲ ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተከብሯል ።
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE