• Call Us
  • +251..........

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የወላይታ ሶዶ ከተማን የማዘጋጃ ቤታዊ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ በይፋ አስጀመሩ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የወላይታ ሶዶ ከተማን የማዘጋጃ ቤታዊ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ በይፋ አስጀመሩ   

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የወላይታ ሶዶ ከተማን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ዲጂታላይዝ በማድረግ ማዘመን የሚያስችል የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ በከተማው ማዘጋጃ ቤት በመገኘት በይፋ አስጀምረዋል፡፡  

በክልሉ ከሚገኙ የረጂዮ ፖሊስ ከተሞች አንዱ የሆነው የወላይታ ሶዶ ከተማን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ዲጂታላይዝ ማድረግ መቻሉ የተቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥና ዘመናዊ አሰራር በመዘርጋት የከተማውን ዕድገት በማፋጠን ከተማው የሚጠበቅበትን የመሪነት ሚና እንዲጫወት ያስችለዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የክልሉ መንግስት የከተሞችን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን በተቀላጠፈ አሰራር ዘርፈ ብዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመቅረፍ ባለፈ የከተሞች ተወዳዳሪነትንና ተመራጭነትን በማስፋት ቀጣይነት ያለው ዕድገት ማስመዝገብ የሚያስችሉ ውጤታማ የሪፎርም ስራዎች በመስራት ላይ ይገኛል፡፡