በጌዴኦ ዞን የኢኮኖሚ ፎረም እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ የኢኮኖሚ ፎረም እየተካሄደ ይገኛል።
በፎረሙ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አበባየሁ ታደሰን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የጌዴኦ ተወላጅ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል ።
በዚህም ፎረም በዞኑ ያለውን የኢኮኖሚ አቅም በሚገባ መጠቀም የሚያስችል ውይይት እንደሚደረግ ተመላክቷል።
በዞኑ ተወላጆች እየተካሄደ ያለዉ ይህ ፌረም ፣ከግሉ ዘርፎች ጋር በጋራ ትበብርና መፍትሔ ለማበጀት አጀንዳዎችን ለመቅረጽና የሚያስችል ነው ተብሏል ።
በፎረሙ ፣የኢኮኖሚ ዘርፍ ምሁራን ቡና አቅራቢዎች እና ተጋባዥ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ዜጎች እየተሳተፉ ይገኛል።
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE