• Call Us
  • +251..........

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በምዕራብ አባያ ማሰልጠኛ ተቋም ያሰለጠናቸውን 1ኛ ዙር ምልምል ፖሊሶች የምረቃ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በምዕራብ አባያ ማሰልጠኛ ተቋም ያሰለጠናቸውን 1ኛ ዙር ምልምል ፖሊሶች የምረቃ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በምዕራብ አባያ ማሰልጠኛ ተቋም ያሰለጠናቸውን 1ኛ ዙር ምልምል ፖሊሶች የምረቃ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት አባላት በሙያ ስነ ምግባር ታንፀውና ሕዝባዊ ቅቡልነት እንዲኖረው እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል ።

በዚህም ዛሬ የሚመረቁ ምልምል ፖሊሶች፣መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠና በመዉሰድ፥የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ አቅም የሚሆኑ ናቸው ።

ከተመረቁት መካከል ከ5መቶ 99 በላይ የሚሆኑት መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠና እንዲሁም፤ ከ63 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በፖሊስ ፋዉንደሽን ውስጥ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የወሰዱት ይገኙበታል ።

በምረቃው ስነስርዓት ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ ፤የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።