• Call Us
  • +251..........

ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ውጤታማ ውይይቶች አድርገናል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ውጤታማ ውይይቶች አድርገናል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ውጤታማ ውይይቶች ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድን ሸኝቻለው ሲሉ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ በይፋዊ ጉብኝታቸው ወቅት የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻችንን ለማጠናከር ውጤታማ ውይይቶችን አድርገናል ነው ያሉት።