• Call Us
  • +251..........

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ

South Ethiopia Regions Government Communications Bureau

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል:-                           

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቀድሞ በደቡብ ብሔር፤ ብሔረሠቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት አካል የነበሩና የህዝቦችን ጥያቄና ፍላጎት መሰረት አድርገው በአዲሱ ከተደራጁት የሲዳማ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ክልሉ የኢፌድሪ ህገመንግስት በሚፈቅደው የክልሎች አደረጃጀት መሰረት በስሩ 12 ዞኖችን እና 95 ወረዳዎችን ይዞ የተቋቋመ ክልል ነው፡፡

የመንግስት አደረጃጀቱም የህዝቦችን መብቶችና የመልካም አስተዳደር ፍላጎቶች ለሟሟላት በሚያስችል መልኩ የህግ አውጭ፤ የህግ ተርጓሚና አስፈጻሚ አካላት ያሉት ሲሆን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲሁም የመንግስት አገልግሎቶች ተደራሽነት ይረጋገጥ ዘንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በስድስት ብዝሃ-ማዕከላት ወላይታ-ሶዶ  የክልሉ የፖለቲካና የአስተዳደር ዋና ማእከል፤ እንዲሁም አርባ ምንጭ የህግ አውጭና የኢኮኖሚ ክላስተር ማእከል፣ ሳውላ የህግ ተርጓሚና የፍትህ ተቋማት ክላስተር ማእከል፣ ካራት የህገመንግስት ትርጉም ማእከል፣ ጂንካ የማህበራዊ ክላስተር ማእከል እና ዲላ የግብርናና የገጠር ልማት ተቋማት ማእከል  በመሆን እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ

 

 

ራዕይ

በ2022 በመረጃ የበለጸገ እና በሀገሩ ላይ መልካም ገጽታን የተጎናጸፈ ዜጋ ተፈጥሮ ማየት፤

 

 

 

 

ተልዕኮ

ሁሉአቀፍና አዳዲስ የኮሚዩኒኬሽን መገናኛ ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶችን እንዲሁም የኢንቨስትመንት መረጃዎችን የሚሰጥ በጥናትና ምርምር የታገዘ አካታች የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ምቹ አካባቢ መፍጠር ነው፡፡

 

 

 

 

ዕሴቶች

√ ቅንነት

√ ታማኝነት

√ ተጠያቂነት

√ የላቀና አሰተማመኝ አገልግሎት መስጠት

√ የፈጠራና የኃሳብ አመንጭነት አቅምን ማዳበር

√ አክብሮትና አንድነት

√ በኃሳብ አሸናፊነት ማመን

√ ትብብርና የቡድን ስራ

√ የአመራር ብቃት

√ ኃላፊነትን መውሰድ

 

 

 

 

ተገልጋዮች

√ መንግስት

√ ሚዲያ

√ ህብረተሰብ

√ ሲቪክ ማህበራት

√ የፖለቲካ ድርጅቶች

√ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች

√ የጥናትና ምርምር፣ ተቋማት

√ የማስታወቂያና የህትመት ሚዲያ አገልግሎት ሰጪዎች

 

 

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ