ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ እንኳን ለከተራ እና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!
ጥምቀት ፍጥረታትን የፈጠረው አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከዮሐንስ ዘንድ የተጠመቀበት የትህትና መገለጫ በዓል ነው።
ኃይማኖታዊ እሴቱንና ትውፊቱን ጠብቆ የሚከበረው የጥምቀት በዓል፤ ከከተራው ጀምሮ አብሮነት፤ አንድነት፣ ፍቅር እና ትህትና የሚንፀባረቅበት ደማቅ በዓል ነው።
ብርሃነ ጥምቀቱ ክርስቶስ የትህትናን ኃያልነት በተግባር ያስተማረበት በመሆኑ፤ በዓሉን ስናከበር በአስተምሮው መሰረት ትህትናን ተላብሰን ዝቅ ብለን ለማገልገል፤ ለመተባበር እንዲሁም ለአንድነትና ለሰላም ለመትጋት ራሳችንን በማዘጋጀት እንደሚሆን ይጠበቃል።
በመሆኑም እኛ የክርስቶስን የፍቅርና የአንድነት ተምሳሌትነት በመከተል፤ መተሳሰብንና በጎነትን ይበልጥ በማጎልበት፤ የተቸገሩትን በመርዳት እንዲሁም በአንድነት ለሁለንተናዊ ዕድገት የድርሻችንን ለመወጣት ቃል በመግባት ማክበር ይገባናል፡፡
በአደባባይ ከሚከበሩ በዓላት አንዱ የሆነዉ ጥምቀት ከኃይማኖታዊ ይዘቱና ሥርዓት በተጨማሪ በዓለም የሰው ልጅ የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ የጋራ ሀብታችን በመሆኑ፤ በዓሉ ኃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል፡፡
በዓሉ የሀገራችንን መልካም ገፅታ ለዓለም የምናሳይበት በመሆኑ፤ መላው የሀገራችን ብሎም የክልላችን ህዝቦች በዓሉን ለመታደም ከተለያየ የዓለም ጫፍ የሚመጡ እንግዶችን በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በፍቅር በመቀበል፤ በትህትና እንድታስተናግዱ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።
ፈጣሪ ሀገራችን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ርዕሰ መስተደድር ጥላሁን ከበደ
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE