በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተፋሰስ ልማት ስራ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ
ጥር 15 /2017 ዓ.ም
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የዘንድሮውን ክልላዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ማብሰሪያ መርሃ ግብር በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ እያካሄዱ ይገኛል።
መርሐግብሩ "የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን!" በሚል መሪ ቃል ለ30 ተከታታይ ቀናት የሚከናወን መሆኑም ተጠቁሟል።
በማብሰሪያ መርሃ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትን ጨምሮ ከፍተኛ የክልልና የዞን አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛል።
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE