"ሀይሶት ህርባ" የጋርዱላ ዞን ህዝቦች ያለፈውን አዝመራ ሰብስበው ፈጣሪያቸውን የሚያመሰግኑበት፣ለቀጣይ የዘር ወቅት የሚዘጋጁበት የደስታና የምስጋና በዓል ነው :- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጋርዱላ ዞን ህዝቦች የዘመን መለወጫ በዓል ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት "ሀይሶት ህርባ" የጋርዱላ ዞን ህዝቦች ያለፈውን አዝመራ ሰብስቦ ፈጣሪያቸውን የሚያመሰግኑበት፣ ለቀጣይ የዘር ወቅት የሚዘጋጁበት የደስታና የምስጋና በዓል ነው ብለዋል።
ባለሰባት ኖታ ፊላ የትንፋሽ መሳሪያን ሰርታችሁ ለአለም እንዳስተዋወቃችሁ በፍቅርና በሰላም ተደምራችሁ ለሀገር ብልፅግና የበኩላችሁን ልታበረክቱ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።
ባለፉት ጊዜያት በዞኑ የነበረውን የሰላም እጦት አስወግዳችሁ በዓሉን በድምቀት በአደባባይ በማክበራችሁ ምስጋና ይገባችኋል ሲሉም ተናግረዋል።
"ሀይሶት ህርባ" በርካታ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን የተጣላ የሚታረቅበት፤ቂምና ቁርሾ የሚወገድበት፣ በድንቅ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የሚታወቅ፣ እህልን በጉድጓድ ለሩብ ምዕተ አመታት በማኖር ቁጠባን የሚያስተምር ድንቅ እሴት መሆኑንም አብራርተዋል።
የጀመራችሁትን የሰላም ግንባታ በማፅናት፣ ልማት ባሻገር በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራና በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መረባረብ ይገባል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን መልዕክት አስተላልፈዋል ።
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE