የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ነው
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል።
ምክር ቤቱ በስብሰባው የግብርና ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚያዳምጥ ሲሆን፤ ሁለት የብድር ስምምነቶችን መርምሮ እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።
የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እንዲሁም የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።
በተጨማሪም የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
Copyrights 2021. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE